የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የስነ-ምግባር ጥፋት በፈጸሙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የፌዴራል ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››› የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የዲሲፕሊን ክስ በቀረበባቸው አስራ ሁለት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና በአንድ ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ በዳኞች ስነ ምግባር ኮሚቴ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ክሶች ዙሪያ ተወያይቶ አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስተራር በፈጸሙት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ከስራ […]