Federal Judicial Administration Council Secretariat

የፍትሐብሄር ጉዳዮች ሙግት እና ማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ላይ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››

የፍትሐብሄር ጉዳዮች ሙግት እና ማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ላይ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ክቡር አቶ ተሾመ ሽፈራው እና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ እንዳለ ታደሰ ሲሆኑ የፍትሐብሄር ጉዳዮች ሙግት እና ማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ላይ በቂ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሌላ መልኩ የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የሁለቱም ፌደራል ፍርድ ቤቶች ክቡሯን ዳኞች የፍትሐብሄር ጉዳዮች ሙግት እና ማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ላይም ሆነ ሌሎች ከስራቸው ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የአጭርና ረዥም ጊዜ ስልጠና መስጠታቸው አቅማቸውን ከማሳደግ ባለፈ የስራ አፈጻጸማቸውን ለመጨመር አወንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የፍትሐብሄር ክርክር የመስማት ሂደቶች ሁለት ደረጃዎች ያላቸው መሆኑን እና የመጀመሪያው ቅድመ ክስ መስማት ዳኞች ተከራካሪ ወገኖችን ግልጽ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የሚደረግበት እና ጭብጥ የመመስረትበት ሂደት ሲሆን ሙግት የመስማት ሂደት ደግሞ በተመሰረቱ ጭብጦች ላይ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት እና ማስረጃ የሚሰማበት መሆኑን ሆኖም በህጉ አተገባበር ላይ ልዩነት በመኖሩ ይህንኑ ልዩነት በማጥበብ የፍትሐብሄር ክርክሮችን ህግን መሰረት በማድረግ መምራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል::ከዚሁ በተጨማሪ የዳኞች

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው