Federal Judicial Administration Council Secretariat

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የስነ-ምግባር ጥፋት በፈጸሙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የፌዴራል ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የዲሲፕሊን ክስ በቀረበባቸው አስራ ሁለት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና በአንድ ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ በዳኞች ስነ ምግባር ኮሚቴ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ክሶች ዙሪያ ተወያይቶ
 አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስተራር በፈጸሙት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ከስራ እንዲሰናበቱ፤
 ሁለት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች እና ሶስት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች መልስ እንዲያቀርቡ፤
 አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና አንድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እንደቅደም ተከተላቸው የጽሁፍና የቃል ማስጠንቀቂያ፤
 አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና አንድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ፤
 አንድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ሲባሉ አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረበባቸው      አቤቱታ አያስጠይቅም ሲል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በሌላ መልኩ አንድ የመሰየም ጥያቄ ያቀረቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጥፋተኛ ከተባሉበት ጊዜ ጀምሮ ያላቸውን ስነምግባርና የስራ አፈጻጸም መርምሮ መልካም ስማቸው ተመልሶ እንዲሰየሙ ጉባኤው ወስኗል፡፡