Federal Judicial Administration Council Secretariat

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቀረቡ የዲሲፕሊን መዝገቦች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

*********************

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል ዳኞች የስነ ምግባር ጉዳዮች ኮሚቴ መርምሮ ባቀረባቸው የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ የስነ ምግባር ደንብ ጥሰት አቤቱታ በቀረበባቸው 10 የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ላይ መልስ እንዲሰጡ ውሳኔ አስተላለፏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክስ የቀረበባቸው ሌሎች ሁለት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የቀረበባቸው አቤቱታ የማያስከስስ ነው በማለት ወስኗል፡፡

በሌላ መልኩ ጉባኤው ከዚህ በፊት በነበሩ አመታት የተከማቹ የዲሲፕሊን ክሶችን ውሳኔ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ሲሆን በሂደት ላይ ያሉ የክስ መዝገቦች በተፋጠነ ሁኔታ እልባት ማግኘት እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው