የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ተግባራት
- የተቋሙን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምራት፣ መቆጣጠርና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ያወጣል፣ ያደራጃል፣ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፡፡
- የበጀት ጥያቄ እና አፈጻጸም ሪፖርቶች በወቅቱ መቅረባቸውን ይከታተላል፣ የአሰራር ማሻሻያዎችን ይቀይሳል ፈርሞ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
- አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችን እና የሰው ሃይል እንዲሟላ ያደርጋል
- የሰራተኞችን የስራ ዕቅድ አፈጻጸም በመሙላት ለሚመለከተው አካል ይልካል
- የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ቡድኖችና ባለሙያዎች የሚበረታቱበትን አሰራር ያመቻቻል
- ከየዘርፉ የሚቀርቡ የግዥና የክፍያ ጥያቄዎችን አስፈላጊነት በማጥናት የግዢ ሰነዶች፣ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎችን በፊርማው ያጸድቃል፣