Federal Judicial Administration Council Secretariat

የለውጥና መልካም አስተዳደር  ዳይሬክተር

  • የሥራ ዘርፉን ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በማድረግ ዓመታዊ እቅድ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
  • የሥራ ዘርፉን በአስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟሉ በማድረግ ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ያደርጋል፣
  • በሥሩ ያሉ ሠራተኞችን ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣
  • የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ውጤታማ የሆኑ ሠራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሠራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
  • ወቅታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
  • የመ/ቤቱን የሥራ ቅልጥፍና፣ ውጤታማነትንና፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮችን ለመዘርጋት የሚያስሉ ተከታታይ ጥናቶችን ያቅዳል፣ ይመራል፣