Federal Judicial Administration Council Secretariat

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ መልእክት

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 684/2002 የተቋቋመ ሲሆን ከዚያም በፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 ሰፊ ሃላፊነት እና ተግባራት እንዲኖሩት ተደርጎ ተቋቁሟል፡፡የጉባኤ ጽ/ቤቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት እዉቅና የተሰጠዉን ተቋማዊ እና ግለሰባዊ የዳኝነት ነጻነትን፤ገለልተኝነት እና ተጠያቂነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለበት ሲሆን ይህንንም የሚያሳካዉ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 የተሰጠዉን ሃላፊነት በመወጣት እና የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሚያወጣቸዉን ህጎች፤መመሪያዎች እንዲሁም ዉሳኔዎችን በማስፈጸም እና በመከታተል ነዉ፡፡

የጉባኤ ጽ/ቤቱ በፌደራል ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች ላይ የሚቀርቡ የዲስፕሊን ክሶችን የመቀበል፤የቀረቡትን ክሶች በማደራጀት ለፌደራል ዳኞች ስነ ምግባር ኮሚቴ የመምራት፤በዳኞች ስነ ምግባር ኮሚቴ የዉሳኔ ሃሳብ የቀረበባቸዉን የዲስፕሊን ጉዳዮች ለፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የማቅረብ እና የዲስፕሊን ክሶችን በተመለከተ በጉባኤዉ የተሰጡ ዉሳኔዎችን የማስፈጸም እና አፈጻጸማቸዉን መከታተል ነዉ፡፡

ክቡር አቶ ቡላ ዋጋሪ ቦርቶላ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ

********************* የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል ዳኞች የስነ ምግባር ጉዳዮች ኮሚቴ መርምሮ ባቀረባቸው የውሳኔ …

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››› የፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማትን በተመለከተ ለፌደራል መጀመሪያ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሄር ችሎት ዳኞች ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል …

››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››› የፍትሐብሄር ጉዳዮች ሙግት እና ማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ላይ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም …

››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››› የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መጋቢት 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የስነ-ምግባር ግድፈት በፈጸሙ አምስት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና በአንድ …

Select የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቀረቡ የዲሲፕሊን መዝገቦች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቀረቡ የዲሲፕሊን መዝገቦች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ Select …

What Our Directors Say

ለተገልጋይ ማህበረሰብ፡-
የፌዴራል ዳኞች ፍርድ ሥራዎች ምርመራ እና ዲሲፕሊን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዳኝነት ተጠያቂነት መርህ ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እሴቶች መሠረት ያደረገ እና የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሠ የዳኝነት አካል እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በ2016 ዓ/ም ዳይሬክቶሪቱ በተሰጠው ተግባራት እና ኃላፊነት መሠረት የሚቀርቡትን የዲሲፒሊን ክስ በመቀበል አቤቱታዎችን በማደራጀት ከፈዴራል ዳኞች የሥነ-ምግባር እና ዲሲፕሊን ኮሜቴ ጋር በጋራ በመሆን በርካት የስነ- ምግባር ጉዳዮች በመስራት የተሸለ ውጤት ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡
ስለሆነም በቀጣዩ ጊዜ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በአካል ይዞ ከመቅረብ ባለፈ ባአሉበት በመሆን የተቋሙን ዌይብ ሳይት በመጠቀም አቤቱታዎችን በማቅረብ ተገቢውን አገልግሎት ሆነ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

አቶ ሀብታሙ ገ/ፃደቅ
የፌዴራል ዳኞች ፍርድ ሥራዎች ምርመራ እና ዲሲፕሊን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የኢትዮጵያ ፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ዋና ሚና በማህረሰቡ ውስጥ ቀልጣፋ የዳኝነት ሥርዓት መዘርጋትና ማስቀጠል ነው። ይህም የዳኞችን ሹመት እና ከስልጣን መውረድን፣ የዳኝነት ስራዎችን መቆጣጠር፣ የትምህርት መርሃ ግብሮችን መስጠት፣ የፋይናንስ ሀብቶችን ማስተዳደር እና እየተሻሻሉ የህግ ማዕቀፎችን ለማስማማት ፖሊሲዎችን ማዘጋጀትን ይጨምራል። ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና በዜጎች መካከል መተማመን እና እርካታ እንዲሰፍን ከህዝብ ጋር መስተጋብር መፍጠር ዋና ተግባር ነው። እነዚህን አላማዎች ለማሳካት ቀጣይነት ያለው ተሃድሶ የግድ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ዋና አካል የሆነው የተሃድሶና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ይህንን ወሳኝ አጀንዳ ይመራዋል። የዳይሬክቶሬቱ ኃላፊነቶች የአካልና የበጀት እቅድ እና ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣ የዳኞች እና የሰራተኞች የስራ አፈጻጸም ክትትል፣ የዕድገት ግምገማ እና የቀጣይ የስልጠና መርሃ ግብሮችን እና ፕሮጄክቶችን ለመቅረጽ ግብረመልስን መጠቀምን ያጠቃልላል። በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረኮች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ተቋሙ ተገቢውን የማሻሻያ ስልቶችንና አሠራሮችን ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው። በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የተቋሙን ተልእኮ እና ራዕይ ለታታሪ ባለድርሻ አካላት፣ ለአገልግሎት ተጠቃሚዎች እና ለሰፊው ህዝብ በትጋት ያስተላልፋል።

የተሃድሶ እና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክተር እንደመሆናችን መጠን ጠንካራ አጋርነት ለመፍጠር፣ ትብብርን ለማጎልበት እና ጠንካራ ግንኙነትን ለመተግበር ያለንን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በእርግጠኝነት ማጉላት አስፈላጊ ነው።

አቶ ሙላቱ ገብሩ
የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር

የዳኞች መኖሪያ ህንጻ