Federal Judicial Administration Council Secretariat

ዳይሬክተሮቻችን ምን ይላሉ

በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዳኝነት ተጠያቂነት መርህ ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እሴቶች መሠረት ያደረገ እና የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሠ የዳኝነት አካል እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በ2016 ዓ/ም ዳይሬክቶሪቱ በተሰጠው ተግባራት እና ኃላፊነት መሠረት የሚቀርቡትን የዲሲፒሊን ክስ በመቀበል አቤቱታዎችን በማደራጀት ከፈዴራል ዳኞች የሥነ-ምግባር እና ዲሲፕሊን ኮሜቴ ጋር በጋራ በመሆን በርካት የስነ- ምግባር ጉዳዮች በመስራት የተሸለ ውጤት ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡
ስለሆነም በቀጣዩ ጊዜ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በአካል ይዞ ከመቅረብ ባለፈ ባአሉበት በመሆን የተቋሙን ዌይብ ሳይት በመጠቀም አቤቱታዎችን በማቅረብ ተገቢውን አገልግሎት ሆነ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

አቶ ሀብታሙ ገ/ፃደቅ

የፌዴራል ዳኞች ፍርድ ሥራዎች ምርመራ እና ዲሲፕሊን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
  • የተቋሙን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምራት፣ መቆጣጠርና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
  • የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ያወጣል፣ ያደራጃል፣ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፡፡
  • የበጀት ጥያቄ እና አፈጻጸም ሪፖርቶች በወቅቱ መቅረባቸውን ይከታተላል፣ የአሰራር ማሻሻያዎችን ይቀይሳል ፈርሞ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ 
  • አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችን እና የሰው ሃይል እንዲሟላ ያደርጋል
  • የሰራተኞችን የስራ ዕቅድ አፈጻጸም በመሙላት ለሚመለከተው አካል ይልካል
  • የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ቡድኖችና ባለሙያዎች የሚበረታቱበትን አሰራር ያመቻቻል
  • ከየዘርፉ የሚቀርቡ የግዥና የክፍያ ጥያቄዎችን አስፈላጊነት በማጥናት  የግዢ ሰነዶች፣ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎችን በፊርማው ያጸድቃል፣

አቶ ደረጀ ቦጋለ

የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር