Federal Judicial Administration Council Secretariat

በፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማት ላይ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››

የፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማትን በተመለከተ ለፌደራል መጀመሪያ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሄር ችሎት ዳኞች ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ ብርሃኑ መንግስቱ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ ሙሉሰው ድረስ ሲሆኑ በፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማት ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የፍትሐብሄር ችሎት ዳኞች የፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማትን በተመለከተ በህጉና አተገባበሩ ያለውን ክፍተት ተገንዝበው በፍትሐብሄር ህጉ በተደነገገው ስርዓት መሰረት መካሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ መልኩ የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የፌደራል መጀመሪያ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የፍትሐብሄር ክርክር ቅድመ ክስ መስማትና መሰል ስልጠናዎችን መመቻቸታቸው የፍትሐብሄር ችሎት ዳኞችን አቅም ለማሳደግ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው