የፌደራል ዳኞች ጥቅማጥቅም ስልጠናና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር
- የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣
- ከጽ/ቤቱ ስትራቴጂክዊ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
- ዳኞች የሚገባቸውን ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ ጥናትናምርምሮችንያካሄዳል፣በጥናት የተደገፈ የውሳኔ ሐሳብ ለጉባኤው ጽ/ቤት ያቀርባል፣
- የዳኞችጥቅማጥቅም፤ሌሎች የአስተዳደር ጉዳዮች የተሟላ የህግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፣አስተዳደራዊ ስራዎች በአግባቡ መፈጸማቸውን ይከታተላል፡፡
- የዳኞች ምልመላ በተመለከተ መመሪያዎችንና ማንዋሎችን አዘጋጅቶ እንዲጸደቅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
- የእጩ ዳኞች ምልመላ ከምዝገባ እስከ ሹመት ድረስ ያለውን ሂደት ይካታተላል
- የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ተሞክሮችን ይዳስሳል፤ጠቃሚ የሆኑትን በስራ ላይ እንዲውሉ ይደርጋል
- በተቋም ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ያደርጋል፣ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችና አገልግሎቶች ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ እንዲሁም ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲኖር ያደርጋል፣
- አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
- የተቋም ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣
- በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት በተቋሙ ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፡፡
- በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
- የዳኞች እና የሠራተኞች የግል ማህደሮች ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ያደርጋል፣
- የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ የሚያደርግ ስርዓት ይዘረጋል፣በአግባቡ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የሠራተኞችን እና የዳኞች አጠቃላይ እስታስቲካዊ መረጃዎች መያዙን ይከታተላል
- ወቅታዊ የስራ አፈጻጻም ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
- ከሌሎች የጽ/ቤቱ የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር ይሠራል፣