የፍርድ ሥራ ምርመራ እና የዳኞች ዲሲፕሊን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተግባራት
በዳኞች ላይ የቀረቡ የዲሲፕሊን አቤቱታዎችን ይቀበላል፤
የቀረቡትን የዲሲፕሊን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ ቅሬታ የቀረበባቸውን መዛግብት ከየ ፍርድ ቤቶች መዝገብ እንዲመጣ ያደርጋል፤
መዝገቦች በጥንቃቄ መያዛቸውንና መመለሳቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤
የዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች የስነ ምግባር መረጃ ይይዛል፤በሚመለከተው አካል ሲጠየቅ ይሰጣል፡፡
የፌደራል ዳኞች የስነምግባርና ዲሲፕሊን ጉዳዮች ኮሚቴ ተግባር
በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት አማካኝነት የሚቀርቡለትን የዲሲፕሊን መዛግብት ቅሬታውንና ቅሬታ ከቀረበበት የፍርድ ቤት መዝገብ ጋር ምርመራ በማድረግ በፌደራል ዳኞች የሥነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ክስ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ቁጥር 3/2014 አንቀጽ 25 (3) (ሀ) መሠረት የምርመራ ሪፖርት /የውሳኔ ሃሳብ ለፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ያቀርባል::