Federal Judicial Administration Council Secretariat

ራዕይ

በ2017 ተቋማዊ አቅሙ የዳበረ፣ የላቀ የዳኝነት ነፃነትና ተጠያቂነትን ለማስከበር ብቃት ያለው እና የህዝብ አመኔታ ያተረፈ ተቋም ሆኖ መገኘት፤

ተልዕኮ

ብቃት ያላቸውን ዕጩ ዳኞች በገለልተኝነትና በጥራት በመመልመል፤የዳኞችን ስነምግባርና የሥራ አፈጻጸም ምዘናን በቀጣይነት በመከታተል አቅማቸውን እንዲሻሻል በማድረግ ምቹ የዳኝነት የስራ ሁኔታ ተፈጥሮ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ውጤታማ፣ ነፃና ተጠያቂ የዳኝነት ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ፤

እሴቶች

• ታማኝነት
• የዳኝነት ነጻነት
• ህግ አክባሪነት
• ራስን ማብቃት
• ገለልተኝነት
• ተጠያቂነት
• ውጤታማነትess;

የጉባኤው ጽ/ቤት ተግባር እና ኃላፊነት

የጉባዔው ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተግባራት እና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1. የጉባኤውን ዓመታዊ የሥራ እቅድና በጀት ማዘጋጀት፤ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳደራል፤
2. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 38 መሰረት በፌደራል ዳኞች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በመቀበል ለሚመለከተው ኮሚቴ መምራት፤በአቤቱታዎቹ ላይ ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል፤
3. በጉባኤው የተወሰኑ ውሳኔወች በሰብሳቢዉ ፊርማ ለሚመለከተዉ አካል እንዲደርስ ማድረግ፤ ዉሳኔዎቹ መፈጸማቸዉን ይከታተላል፤
4. የፌደራል ዳኞች የግል ማህደርን ማደራጀት፣ አስፈላጊ መረጃዎችም በማህደሮቹ መግባታቸውን መከታተል፣ የግል ማህደሮች በሚመለከተው ኮሚቴ ሲፈለጉ ያቀርባል፤
5. የጉባኤውን እና የኮሚቴዎችን የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን ሌሎች ሰነዶችን በአግባቡ አደራጅቶ ይይዛል፤
6. በጉባኤው በሚቋቋሙ ኮሚቴዎች ውስጥ በቋሚነት የሚያገለግሉ ከኮሚቴው ኃላፊነት ጋር ተዛማጅ እውቀት እና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በቋሚነት መመደብ፤ሥራቸውንም ይከታተላል፤
7. የዳኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ጉባኤው በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በፍርድ ቤቱ አስተዳደር በቋሚነት መከናወኑን ያረጋግጣል፤
8. የፌደራል ዳኞችን አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች እና ባለሙያዎች ጋር በመሆን አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
9. ዳኞች ሙያቸዉን እንዲያዳብሩ የተለያዩ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል።