Federal Judicial Administration Council Secretariat

ስለ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ተጨማሪ ይወቁ

ስለ ጽ/ቤታችን

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የአደረጃጀት ታሪክ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ከወጣው የአዋጅ ቁጥር 323/1965 ይጀምራል፡፡   በዚህ አዋጅ  ዳኞችን የመምረጥ ፤የዳኞችን የዓመት ፈቃድ ዳኞችን የማዘዋወር፣የዳኞችን ደረጃ የማውጣት፤ የዳኞች ዲሲፕሊን እና የአፈጻጸም ጉድለቶች  ላይ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን በግልጽ ተለይቶ ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ  የተሰጠ ሲሆን አባላቱ የነበሩት የፍርድ ሚኒስቴሩ፤ አፈንጉሱ፤ የመንግስት ሰራተኞች ማስተዳደሪያና የጡረታ  ጉባዔ የበላይ ኮሚሽነር፤ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ጠቅላይ ዓ/ህግ ና በንጉሱ የሚሾሙ ሁለት  ሰዎችን በአባልነት ያቀፈ ሆኖ ጸሀፊው ከፍርድ ሚኒስቴር እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡  በአጠቃላይ አዋጁ ዳኞች ስራቸውን  በሙሉ ነጻነት እንደሚያከናውኑ ቢገልጽም ከአባላት ስብጥር እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮችን ለአስፈጻሚው እና ለንጉሠ ነገሥቱ አሳልፎ የሚሰጥ የነበረ  በመሆኑ ጉባዔው የታለመለትን  ዓላማ ሊያሳካ አልቻለም፡፡

ራዕይ

በ2017 ተቋማዊ አቅሙ የዳበረ፣ የላቀ የዳኝነት ነፃነትና ተጠያቂነትን ለማስከበር ብቃት ያለው እና የህዝብ አመኔታ ያተረፈ ተቋም ሆኖ መገኘት፤

ተልዕኮ

ብቃት ያላቸውን ዕጩ ዳኞች በገለልተኝነትና በጥራት በመመልመል፤የዳኞችን ስነምግባርና የሥራ አፈጻጸም ምዘናን በቀጣይነት በመከታተል አቅማቸውን እንዲሻሻል በማድረግ ምቹ የዳኝነት የስራ ሁኔታ ተፈጥሮ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ውጤታማ፣ ነፃና ተጠያቂ የዳኝነት ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ፤

እሴቶች

• ታማኝነት
• የዳኝነት ነጻነት
• ህግ አክባሪነት
• ራስን ማብቃት
• ገለልተኝነት
• ተጠያቂነት
• ውጤታማነት